Thursday 30 April 2015

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በሊቢያ ሀገር በንጹሐን ወገኖች ላይ ስለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ከእኩለ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ የዜና ማሰራጫዎች በሰሜን አፍሪካ በሊቢያ የሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ አካባቢ አይኤስ በተባለ አሸባሪ ቡድን በንጹሐን ወገኖች አሰቃቂ ግድያ እንደተፈጸመባቸው ዘግበዋ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 
 ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ከእኩለ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ የዜና ማሰራጫዎች በሰሜን አፍሪካ በሊቢያ የሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ አካባቢ አይኤስ በተባለ አሸባሪ ቡድን በንጹሐን ወገኖች አሰቃቂ ግድያ እንደተፈጸመባቸው ዘግበዋል፡፡ ዘገባው ከምኑም ከምኑ የሌሉበት ንጹሐን ክርስቲያን ወጣቶች በታጠቁና ፍጹም ሰብኣዊነት በሌላቸው አሸባሪዎች ሲገደሉ የሚያሳየው ምስልም በመላው ዓለም እየታየ ይገኛል፡፡ አሰቃቂው ግድያ ስለተፈጸመባቸው ንጹሐን ወጣቶች ዜግነትና ማንነት ግልጽና አስተማማኝ የሆነ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በበርካታ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ሲነገር እንደሚሰማው የዚህ የግፍ ወንጀል ሰለባዎች ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መሆናቸውን የዜና ማሰራጫዎቹ አክለው እየገለጹ ነው፡፡ የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፈጣሪ የተሰጠች የማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት ኃላፊነት በማይሰማቸውና በእነሱ ላይ ሊደረግ በማይፈቅዱ ምንም ዓይነት ሰብአዊ ርኅራኄ በሌላቸው እንድትቀጠፍ ስለማትፈቅድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን አሰቃቂ ድርጊት በጽኑ ትቃወማለች፣ አጥብቃም ታወግዘዋለች፡፡ስለዚህ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት ወገኖቻችን ማንነት ተረድተን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን ሕዝበ ክርስቲያኑና መላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ተገንዝበው ሁኔታውን በትዕግሥት እንዲጠብቁ፤ እንደዚሁም የተፈጸመው የጭካኔ ተግባር የማንኛውም ሃይማኖት ተቋምና እምነት የማይወክል የአሸባሪዎች ተግባር መሆኑን ተገንዝበው ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሁሉ እንደቀድሞው በአንድነት በማውገዝ የዚህ ድርጊት ፈጻሚዎች ኪሣራ እንጂ ምንም ዓይነት ትርፍ የማያገኙ መሆናቸውን በተግባር እንዲያሳዩዋቸው እናሳስባለን ፡፡

 እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ 
አሜን 
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
 ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
 አዲስ አበባ
ምንጭ http://www.eotc-patriarch.org/index.php/news

ውዳሴ ማርያም


ቅዳሴ


መልከዓ ኢትዮጵያ


Wednesday 22 April 2015

ግፉዓን ይትማሰጥዋ ለመንግሥተ ሰማያት በሃይማኖታቸው ምክንያት ግፍ የሚደርስባቸው መንግሥተ ሰማያትን ይናጠቋታል፡፡ (ማቴ. 11-12)

በሰሜን አፍሪካ ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ PDF፡፡

Thursday 16 April 2015

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከግብፁ ፕሬዚዳንት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ

የሕዳሴ ግድብን መሠረት በማድረግ የስምምነት ፊርማ ሱዳን ላይ አድርገው ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ሀገራችን የመጡትና ከሀገራችን ከፍተኛ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ስለ አጠቃላይ የጋራ እሴቶችና የጋር ጥቅሞች አብሮ ተባብሮ ማሳደግ ስለሚቻልበት ሁኔታ እጅግ መልካም በሆነ ሁኔታ ሲነጋገሩና ስምምነት ላይ የደረሱትን የግብፁ ፕሬዚዳንት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትም ውጤታማና ለሁለቱም ሀገራትና ሕዝቦች በሚበጅ ጉዳዮች ዝግ በሆነ መልኩ ውይይት አድርገው የጋራ መግባባት ላይ ደርሷል፡፡
233

የትንሳኤ በዓል አከባበር (2007) Glasgow, Scotland



በቤተ ክርስቲያን ሥዕላት ዙሪያ የውይይት መርሐ ግብር ተካሄደ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የአሳሳል ዘይቤ ጠብቃ ተንከባክባ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለባት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ባዘጋጀው የውይይት መርሐ ግቭር ተገለጸ

ማኅበረ ቅዱሳን ሳምንታዊ የኢንተርኔት ቴሌቪዥን (Online Tv) ሥርጭት ጀመረ

መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍል ሳምንታዊ የኢንተርኔት TV ሥርጭት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ የትንሳኤ በዓልን አስመልከቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

abune matyas 17
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉትን ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

ብርሀነ ህሊና መፅሀፍ

ብርሀነ ህሊና መፅሀፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት

የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ለማንበብ ይህን ይጫኑ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አጭር ታሪክ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አጭር ታሪክ ለማንበብ ይህን ይጫኑ

ቅዱስ ሙሴ ፀሊም ኢትዮጵያዊ ክፍል ፪ - Ethiopian Moses the black: Part 2


ቅዱስ ሙሴ ፀሊም ኢትዮጵያዊ ክፍል ፩ - Ethiopian Moses the black: Part 1


ሰሙነ ሕማማት ክፍል ፭ - HImmamat Part 5


ሰሙነ ሕማማት ክፍል ፬ - Himmamat Part 4


ሰሙነ ሕማማት ክፍል ፫ - Himmamat Part 3


ሰሙነ ሕማማት ክፍል ፪ - Himmamat Part 2


ሰሙነ ሕማማት ክፍል፡፩ - Hemmamat Part 1

ጴጥሮስ ያችን ሰዓት ክፍል፡፬ - Petros at the hour. Part 4


ጴጥሮስ ያችን ሰዓት ክፍል፡፫ - Petros at the hour. Part 3


ጴጥሮስ ያችን ሰዓት ክፍል፡፪ - Petros at the hour. Part 2


ጴጥሮስ ያችን ሰዓት ክፍል፡፩ - Petros at the hour. Part 1


የቅድስት፡ አርሴማ፡ ገድል፡ ፊልም፡ ክፍል፡፮ (6)


የቅድስት፡ አርሴማ፡ ገድል፡ ፊልም፡ ክፍል፡፭ (5)


የቅድስት፡ አርሴማ፡ ገድል፡ ፊልም፡ ክፍል፡፬ (4)


የቅድስት፡ አርሴማ፡ ገድል፡ ፊልም፡ ክፍል፡፫ (3)


የቅድስት፡ አርሴማ፡ ገድል፡ ፊልም፡ ክፍል፡፩ (2)


የቅድስት፡ አርሴማ፡ ገድል፡ ፊልም፡ ክፍል፡፩ (1)


ነቢዩ ሐጌ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 ሐጌ ማለት በዓል፣ ደስታ ማለት ነው፡፡ የስሙ ትርጓሜ ሕዝቡ ከምርኮ የሚመለሱ ስለኾነ ይኽን ደስታ የሚያስረዳ ነው፡፡
 በብሉይ ኪዳን በመጨረሻ የምናገኛቸው ሦስቱን መጻሕፍት ማለትም ትንቢተ ሐጌ፣ ትንቢተ ዘካርያስና ትንቢተ ሚልክያስ ከምርኮ በኋላ ስላለው ጊዜ እንዲኹም አይሁድ ከምርኮ እንዴት ወደ አገራቸው እንደተመለሱ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ በዚያ አንጻር ግን ደቂቀ አዳም ከዲያብሎስ ምርኮ እንደምን ወደ እግዚአብሔር እንደተመለሱ የሚያረዱ ናቸው፡፡
ነቢዩ ሐጌ የተወለደው በምርኮ በባቢሎን ሲኾን ትንቢቱን ሲናገር የ፸፭ ዓመት ሽማግሌ ነበር፡፡ የእስራኤል ቅሪቶች ወደ ኢየሩሳሌም በዘሩባቤል አማካኝነት ሲመለሱ ነቢዩ ሐጌም ከተመለሱት ጋር አንዱ ነበር፡፡


ነቢዩ ዘካርያስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

“ዘካርያስ” ማለት “ዝኩር፣ ዝክረ እግዚአብሔር - እግዚአብሔር ያስታውሳል” ማለት ነው፡፡ ይኸውም በምርኮ የነበሩትን አይሁድ እግዚአብሔር እንዳሰባቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በምስጢራዊ መልኩ ግን እግዚአብሔር ኹል ጊዜ በእኛ ውስጥ ያለችውን ቤተ መቅደስ (ነፍሳችንን) እንድናንፃት እንደሚያሳስበን፣ በመንፈሳዊ ተጋድሎአችን ኹሉ እንደሚረዳን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በዚኽ ስም የተጠሩ ከ፴ በላይ ሰዎች አሉ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ በፄዋዌ አገር በባቢሎን የተወለደ ሲኾን አባቱ በራክዩ በባቢሎን ስለሞተ ከአያቱ ሐዶ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶአል፡፡ በመኾኑም እርሱና አያቱ በዘሩባቤል መሪነት ከመዠመሪያዎቹ ተመላሾች ጋር ከምርኮ ተመልሰዋል /ነህ.፲፪፡፩፣፬፣፯/፡፡ ትንቢቱንም የዠመረው በ፭፻፳ ቅ.ል.ክ. ላይ ነው፡፡ ከነቢዩ ሐጌ ጋር ማለት ነው፡፡

ነቢዩ ሚልክያስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

“ሚልክያስ” ማለት “መልአክ፣ ሐዋርያ፣ መልእክተኛ” ማለት ነው፡፡ ጥር ፰ ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንደሚያስረዳው ነቢዩ ሚልክያስ የተወለደው ሕዝቡ ከፄዋዌ (ከምርኮ) ከተመለሱ በኋላ ነው፡፡ ከሕፃንነቱ አንሥቶም የእግዚአብሔርን መንገድ የሚወድ ነበር፡፡ ሕዝቡም ይኽን አካኼዱን አይተው እጅግ ያከብሩት ነበር፡፡ ይኽን መልካምነቱንም አይተው “ከእግዚአብሔር የተላከ ነው” ሲሉ ስሙን ሚልክያስ ብለው ጠሩት፡፡
ነቢዩ ሚልክያስ ከጸሐፍት ነቢያት የመጨረሻው ነቢይ ነው፡፡ ከሐጌና ከዘካርያስ በኋላም በነቢይነት አገልግሏል፡፡ ከ፬፻፶-፬፻ ቅ.ል.ክ. ላይ እንደነበረም ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ዕዝራና ነህሚያ ቤተ አይሁድን በሚስተካክሉበት ጊዜ ሚልክያስም ተባባሪያቸው ነበር፡፡

ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓል ኹለቱም ታላላቅ ሐዋርያት በሰማዕትነት ያረፉበትን በዓል ነው፡፡ ይኽ ዕለት በየዓመቱ አይለዋወጥም፡፡ የሐዋርያትን ጦም ከጨረስን በኋላ የምናከብረው ነው፡፡ በዚኽ ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴዋም በትምህርቷም ኹሉ እነዚኽን ታላላቅ ሐዋርያት ታነሣለች፤ ታወድሳለች፤ ሰማዕትነታቸውንም ለልጆቿ ታስተምራለች፡፡ ምንም እንኳን በእነዚኽ ሐዋርያት ስም የተሰየመ ቤተ ክርስቲያን በብዛት ባይገኝም በአዲስ አበባ ግን “ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ” የሚባል ቤተ ክርስቲያን አለ፡፡
 ወደ ሰሜኑ የአገራችን ክፍል ስንሔድ ይኽ ዕለት “ሓወርያ” ተብሎ ይጠራል፡፡ ስያሜውም የእነዚኽን ሐዋርያት ሰማዕትነት ለመግለጥና ለማሰብ የተሠጠ ነው፡፡ እረኞች ጅራፋቸውን ገምደው በቡድን በቡድን እየኾኑ ያስጨኹታል፡፡ የጅራፉ ጩኸት የእነዚኽ ሰማዕታት መገረፍ፣ መቁሰል፣ መሰየፍ፣ መሰቃየት፣ መሰቀል የሚያስታውስ ነው፡፡ አባቶቻችን ክርስትናውን ማንበብና መጻፍ ወደማይችለው ማኅበረ ሰብእ ምን ያኽል እንዳሰረጹትም ከዚኽ እንገነዘባለን፡፡ እኛ ግን እንኳንስ ለተማረው ማስተማር ይቅርና አባቶቻችን የሠሩትን እንኳን መጠበቅ አቅቶናል፡፡

 እነዚኽ ኹለቱም ታላላቅ ሐዋርያት የሚያመሳስላቸውም የሚያለያያቸውም ብዙ ነጥብ አለ፡፡ እስኪ አስቀድመን የሚያለያዩአቸውን ነጥቦች በጥቂቱም ቢኾን እንመልከት፡፡

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

     በየዓመቱ መጋቢት 5 የምናከብረው በዓል አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉበት በዓል ነው፡፡ በዚኽ ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴዋም በትምህርቷም ኹሉ እኒኽን ታላቅና ቅዱስ አባት ታነሣለች፤ ታወድሳለች፤ ተጋድሎአቸውንም ለልጆቿ ታስተምራለች፡፡
ሀገራቸው ንሒሳ (ግብጽ) ሲኾን አባታቸው ስምዖን እናታቸውም አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው 30 ዓመታት ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ እኛ አንድ ነገርን ለምነን በእኛ አቈጣጠር ካልተመለሰልን ስንት ቀን እንታገሥ ይኾን? ዛሬ በልጅ ምክንያት የፈረሱ ትዳሮች ስንት ናቸው? ለመኾኑ እግዚአብሔርን ስንለምነው እንደምን ባለ ልቡና ነው? ጥያቄአችን ፈጥኖ ላይመለስ ይችላል፡፡ ያልተመለሰው ለምንድነው ብለን ግን መጠየቅ ይገባናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡- “የምንለምነውን የማናገኘው በእምነት ስለማንለምን ነው፤ በእምነት ብንለምንም ፈጥነን ተስፋ ስለምንቆርጥ ነው” ይላል፡፡ ሰውን ብንለምነው እንደዘበዘብነው፣ እንደ ጨቀጨቅነው አድርጎ ሊቈጥረው ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ግን እንዲኽ አይደለም፡፡ “ለምኑ ታገኙማላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል” ያለን ርሱ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለምና፡፡ የሚያስፈልገን ከኾነ ያለ ጥርጥር ይሰጠናል፡፡ መቼ? ዛሬ ሊኾን ይችላል፤ ነገ ሊኾን ይችላል፤ ወይም እንደ ስምዖንና እንደ አቅሌስያ የዛሬ 30 ዓመት ሊኾን ይችላል፡፡  ጭራሽኑ ላይሰጠንም ይችላል፡፡ አልሰጠንም ማለት ግን ጸሎታችን ምላሽ አላገኘም ማለት አይደለም፡፡ የለመንነው እኛን የሚጎዳን ስለኾነ እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ሲሰጥ ስለ ፍቅሩ፤ ሲነሳም ስለ ፍቅሩ ነውና፡፡

Wednesday 15 April 2015

PALM SUNDAY

Memory Verse: “Hosanna to the Son of David! Blessed is He who comes in the name of the Lord! Hosanna in the highest.” /Matt. 21:9/

Introduction
• The Lord Jesus Christ came into Jerusalem just five days before His crucifixion. This was the beginning of the final week of His work of redemption on earth. This lesson is about this event and what followed in the days of the crucifixion.

The Lesson 

  • The Sunday before Holy week, or Passion Week is known as Palm Sunday or Hosanna. 
  • It is known as Palm Sunday because, on this day, Children and many people received Jesus Christ into Jerusalem holding palm leaves and laying their clothes on the ground, when He came into Jerusalem sitting on a colt of a donkey. 
  •  It is also known as Hosanna, because they received Him singing, “Hosanna to the Son of David! Blessed is He who comes in the name of the Lord! Hosanna in the highest.” /Matt. 21:9/ 

THE RESURRECTION

"He is not here,He is risen,As he said." Matt 28:6.

 Introduction

 • The Resurrection of Jesus Christ is one of the major holidays observed by the many Christians. It is the day when the Lord defeated death, and gave us the hope of our own resurrection. In this lesson, we are going to learn about the events of the resurrection and its spiritual meaning. The Lesson • The Lord Jesus Christ was crucified on a cross on our behalf so that through His pain, we may be healed, and through His death, we may be alive. • After the Jews crucified Him, they let guards stand watchful at His Tomb, because they feared that His disciples may take His body and claim that Jesus was resurrected: “The chief priests and the Pharisees gathered together to Pilate, saying, ‘Sir, we remember, while He was alive, how that deceiver said, “After three days I will rise”. Therefore command that the tomb be made secure until the third day, lest His disciples come by night, and steal Him away…” Matt. 27:63-64 • But, on the third day, on a Sunday, Jesus Christ was risen from the dead. • An angel of the Lord came down and rolled the stone from the tomb. There was a great earthquake when the angel descended from heaven, and the guards fell down with fear.

THE JOY OF GOING TO CHURCH

“I was glad when they said unto me, let us go into the house of the Lord.” Psalm 122:1 King David used to shepherd his father’s sheep when he was a child. He used to play flute and harp for them, but always paid attention to protect them from lions and bear. He was never afraid because he always trusted that God would protect him. King David was very obedient to his father, and took care of his father’s sheep without complaining. Are you obedient to your parents’ like young David? What do you do in your house to help your Mom or your Dad?

ነገረ ማርያም - ክፍል ፫ (3)

(የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት)

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲሳት መምህር


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 ቅድስት ድንግል ማርያምም እስከ ሦስት ዓመት ድረስ በእናት በአባቷ ቤት ውስጥኖራለች፤ ይኽነን በእናት በአባቷ ቤት የነበራትን አስተዳደግ
“Protoevangelium_of_James” (ፕሮቶቫንጊሊዩም ኦፍ ጀምስበሚለውጥንታዊዉ መጽሐፍ ሲገልጽ (ሕፃኗም ከቀን ወደ ቀን በኀይልና በብርታት እያደገችኼደች፤ የስድስት ወር ልጅ በኾነች ጊዜ እናቷ መቆም ትችል እንደኾነ ለማየትመሬት ላይ አቆመቻት፤ ርሷም ሰባት ርምጃ ተራምዳ ወደእናቷ ዕቅፍ ውስጥ ገባች፤እናቷም እንዲኽ አለቻት “ወደ ጌታ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አስክወስድሽድረስ በራስች እንዳትራመጂ አለቻትና በመኝታ ቤቷ ውስጥ ውስጥ የቅድስናስፍራ አበጀችላት… አንድ ዓመት በኾናት ጊዜም ኢያቄም ታላቅ ግብዣ አድርጎካህናቱን፣ ጸሐፈትን፣ ታላቆችንና ሕዝብን ጠራ፤ ከዚያም ኢያቄም ልጁን ወደካህናቱ አቀረባት እነርሱም “አባታችን እግዚአብሔር ሆይ ይኽቺን ልጅ ባርካትበትውልድ ኹሉ የሚጠራ ማብቂያ የሌለው ስምን ስጣት እያሉ ባረኳት፤ ሕዝቡምኹሉ “ይደረግ ይኹን ይጽና አሜን” አሉ፤ ከዚያም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዳትርሱም “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ይኽቺን ልጅ ተመልከት ለዘላለም በሚኖርበፍጹም በረከትም ባርካት” በማለት ባረካት፤ ሐናም ይዛት ወደ ተቀደሰውየማደሪያዋ ክፍል በመውሰድ ጡትን ሰጠቻት…) ይላል፡፡

ነገረ ማርያም - ክፍል ፪ (2)

(የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትውልድ ሀረጓ የተቀደሰ ታሪክ)

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲሳት መምህር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንዳስተማሩትና እንደጻፉት በእናቷ በሐና በኩልያሉ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ጴጥሪቃ ቴክታ ሲባሉ “ወኮኑ ክልኤሆሙጻድቃን ወፈራህያነ እግዚአብሔር ወይትአመንዎ ለአምላኮሙ በጥቡዕ ልብ እንበለኑፋቄ” ይላል (ኹለቱም ሰዎች ደጋጐችና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ያለምንምመጠራጠር በፍጹም ልቡናቸው በአምላካቸው የሚተማመኑ ነበሩ) እነሱምበጊዜው ይኽ ቀራችኊ የማይባሉ ባለጠጎች ነበሩ፤ ከሀብታቸው ብዛት የተነሣወርቁን ብሩን ንደ ዋንጫ እያሠሩ ከላሙ ከበሬው ቀንድ ይሰኩት ነበር፤ ይኽንያኽል አቅርንተ ወርቅ፣ አቅርንተ ብሩር እየተባለ ይቈጠር ነበር የዕንቁ ጽዋ እንኳ፸፣  ያኽል ነበራቸው፡፡

ነገረ ማርያም- ክፍል ፩ (መግቢያ)

በስመ አብ ወወልድወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

  
  ይህ የነገረ ማርያም (Mariology) ትምህርት ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ስላለው የሕይወቷን ዝክረ ታሪክ፣ ስለ እመ አምላክነቷ፣ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ፣ በነገረ ሥጋዌ ስላላት ሱታፌ (ድርሻ)፣ ስለ ንጽሕናዋና ስለ ተሰጣት ክብር የምናጠናበት የሃይማኖት ትምህርት ክፍል ነው፡፡

ትምህርተ ሃይማኖት (ክፍል ዘጠኝ)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

        ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
        አሰሮ ለሰይጣን - አግዐዞ ለአዳም
        ሰላም - እምእዜሰ
        ኮነ - ፍሰሐ ወሰላም
        ውድ የመቅረዝ አንባብያን! እንዴት አላችኁ? የትምህርተ ሃይማኖት ትምህርቱን እየተከታተላችኁ እንደኾነ ጽኑ እምነቴ ነው፡፡ እስከ አኹን ድረስ የትምህርተ ሃይማኖት መግቢያ፣ የሃይማኖት አዠማመርና እድገት፣ ከኹሉም በፊት አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ማወቅ ያለበት ብለን ነገረ ቤተ ክርስቲያን፣ ቅዱስ ትውፊት፣ ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳድ፣ ስለ ዶግማና ቀኖና፤ ስለ እግዚአብሔር መኖርና ስለ ባሕርዩ ጠባያት እንዲኹም ስሙ ማን እንደኾነ ተማምረናል፡፡ ዛሬም ሥነ ፍጥረት ብለን እንቀጥላለን፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋልን ያድለን፡፡ አሜን!!!

ሥነ ፍጥረት
ትርጕም
የፍጥረት መበጀት፣ የተዋበ ፍጥረት /ዘፍ.1፡31/፤ አንድም የፍጥረት መስማማት፣ የተስማማ ፍጥረት ማለት ነው፡፡ አራቱ ባሕርያት በባሕርያቸው የማይስማሙ ቢኾኑም በእግዚአብሔር ጥበብ ይስማማሉና፡፡