Wednesday 15 April 2015

የትምህርተ ሃይማኖት መግቢያ

በስመ አብ ወወልድወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ሃይማኖት” ማለት አምነ፣ አመነ ከሚል የግእዝ ግሥ የወጣ ሲኾን መዝገበቃላታዊ ትርጓሜውም “ማመን፣ መታመን” ማለት ነው፡፡ በምሥጢራዊውትርጕሙ ግን “ሃይማኖት” ማለት ፍጥረትን ኹሉ ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣአንድ እግዚአብሔር እንዳለ፣ ለሚታየውም ለማይታየውም ፍጥረት ሠራዒውናመጋቢው ርሱ ብቻ እንደኾነ፣ ልዩ ሦስትነት እንዳለው፣ በዚኽ አለ በዚኽ የለምየማይባል ምሉዕ በኵለሄ እንደኾነ፣ … ማመን መታመን ማለት ነው፡፡


 “ማመን” ማለትም ይኾንልኛል ይደረግልኛል ብሎ መቀበል፤ ለእግዚአብሔርየሚሳነው ነገር የለም ብሎ ተስፋ ማድረግ፤ አለመጠራጠር ማለት ሲኾን፤መታመን” ማለት ደግሞ ያመኑትን እውነት በሰው ፊት በአንደበት መመስከርናበተግባራዊ ሕይወት መግለጥ ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይኽንበተመለከተ፡- “ይኽም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነበአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምንትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና” ብሎአስተምሯል /ሮሜ.108-10/፡፡ ዳግመኛም በሌላ አንቀጽ፡- “የእግዚአብሔር ጸጋእንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትኹ፥ሌላውም በላዩ ያንጻል” በማለት ከኹሉ አስቀድሞ እምነት እንደሚያስፈልግያስረዳና፤ ቀጥሎም “ማንም ግን በዚኽ መሠረት ላይ በወርቅ ቢኾን በብርምበከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራይገለጣል፤” በማለት ምግባር ትሩፋት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል /1ቆሮ.31012/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የዕብራውያንን መልእክትበተረጐመበት 9ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “እምነት መሠረት ናት፤ ሌሎች ግን ሕንፃናግንብ ናቸው” በማለት ምግባርና ትሩፋት ከመሥራት በፊት እምነትእንደሚቀድም አስተምሯል /.80-81/፡፡
 ስለዚኽ “ትምህርተ ሃይማኖት” ስንል ስለዚኹ ስለምናምነው አምላክየምንማማርበት የትምህርት ዘርፍ ነው ማለት ነው፡፡ “ስለምናምነው አምላክየምንማማርበት የትምህርት ዘርፍ ነው” ሲባል ግን በፍልስፍናና በዚኽ ዓለምእንደምናደርገው በምርምርና በሙከራ እንደርስበታለን ለማለት ሳይኾንእግዚአብሔር ራሱ በተለያየ መንገድ የገለጠውንና እንድናውቀው የፈቀደውን ብቻእንማማራለን ለማለት ነው፡፡ በዚኹ ዙርያ ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር ስንማማርበስፋት እንመለስበታለን፡፡
በፍልስፍናው ዓለም ፍልስፍናን ለመማር የራሱ የኾነ ቅድመ ኹኔታ (Axiom)እንዳለ ኹሉ በትምህርተ ሃይማኖትም ስለ ፈጣሪ ለማወቅ “ወደ እግዚአብሔርየሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድያስፈልገዋል ተብሎ እንደተጻፈ አስቀድሞ እምነት ያስፈልጋል /ዕብ.116/፡፡እምነት ማለትም ለመለኮታዊው መገለጥ የምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡ በትምህርተሃይማኖት የመዠመሪያው ቅድመ ኹኔታ ይኽ እምነት ነው፡፡ እምነት ሳይኖረንትምህርተ ሃይማኖትን መማር አይቻለንም፤ ትምህርተ ሃይማኖት የአዕምሮ ጨዋታአይደለምና፡፡ ትምህርተ ሃይማኖትን ስናጠና ኹል ጊዜ እምነት ሊኖረንያስፈልጋል፡፡ እምነት ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ስጦታ ቢኾንም ፈቃዳችንንይጠይቃል፡፡ ይኽ አካሔድም በቤተ ክርስቲያን ቋንቋ “ፍኖተ አሚን” ይባላል፡፡  
 ቀጥሎ የሚመጣው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “እኛስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅክርስቶስ አንተ እንኾንኽ አምነናል፤ ዐውቀናልም” እንዳለው ዕውቀት ነው /ዮሐ.669/፡፡ ኾኖም አኹንም ጥንቃቄ ያስፈልገናል፡፡ ይኸውም ይኽ ስለ ፈጣሪየምናውቀው እውነት መጨረሻ የለውም፡፡ ለምንእግዚአብሔር ወሰን የለውምና/ኤር.2323/፡፡ ተጠንቶ የሚያልቀው ውስንነት ስላለው አካል (ፍጡርብቻነው፤ ያውም አብዛኛው አያልቅም፡፡ ስለኾነም ስለ እግዚአብሔር የምንማረውኹሉ በጥቂት ቃላት ብቻ ታጥሮ የሚያበቃ አይደለም፡፡ ይኽ አነጋገር በኦሬንታልኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት አነጋገር “Apophatism -አፖፋቲዝም” ይባላል፡፡ በኢ////. “አንድም  አንድምታ” እያልንየምናውቀው ነው፡፡
ታድያ መማራችን ምን ፋይዳ አለው?” የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፡፡
1የተገለጠውን እውነት ለመረዳት ይጠቅማል፤
2የቀደመችውን አንዲቷን መንገድ መያዝ ስለሚያስፈልግ እውነትን ከሐሰትለመለየት ይረዳናል፤
 ምንም እንኳን ክርስትና የመገለጥ ሃይማኖት ቢኾንም፥ ምንም እንኳንእግዚአብሔር ሰዎች ፈልገው የማያገኙት ቢኾንም፥ በመጽሐፍ ቅዱስና በሥነፍጥረት የተገለጠውን ግልጽ ትምህርት መማርን ግን አያወግዝም፡፡ ኹል ጊዜእውነትን ለማወቅ ከመጠየቅ ዕረፍት የሌለው የሰው ልጅ አዕምሮንም በአመክንዮ(By Reason) ማስረዳትን እንዲኹ አያወግዝም፡፡ ይልቁንም አመክንዮንበትክክለኛው መንገድ እንድንጠቀምበት ያግዛል እንጂ፡፡
ተመስጦ

ቸርና ሰው ወዳጅ የኾንከው እግዚአብሔር ሆይካለ መኖር ወደ መኖርያመጣኸን አንተ ነኽ፡፡ ምን እንደሚያስፈልገን ዐውቀኅ የሚጠቅመንን ብቻየምትሰጠን አንተ ነኽ፡፡ ይኽም የምታደርገው ስለ ፍቅርኅ እንጂ ከእኛ መልካምነገር አግኝተኅ አይደለም፡፡ ቅዱስ ሆይእንኪያስ እኛም ፍቅርኅ ይገባን ዘንድልቡናችንን በብርሃንኅ አብራልን፡፡ አምነንና ታምነን እንጸና ዘንድ ርዳን፡፡ በፍኖተአዕምሮ ሳይኾን በፍኖተ አሚን ተጕዘን “ እናንተ የአባቴ ብሩካን፤ ዓለምከተፈጠረበት ጊዜ ዠምሮ የተዘጋጀላችኁን መንግሥት ውረሱ” ብለኅ በቀኝከምታቆማቸው ቅዱሳን ጋር እንቈጠር ዘንድ ቸርነትኅ ትርዳን፡፡ አሜን፤ይኹንልን፤ ይደረግልን፡፡

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 5 ቀን፣ 2007 ..)- 

1 comment:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    ReplyDelete