
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን ሆቴል ተገናኝተው ያደረጉት ውይይት መልካም የሚባሉና ለሁለቱም ሀገር ሕዝቦች ብሎም ለመላው አፍሪካ የሚበጅ አጀንዳዎች በማንሳት መሆኑ ቅዱስነታቸው ከውይይት በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡ የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎችን በተመለከተ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ስለ ዓባይ ግድብ በጋራ መጠቀምን፣ ስለ ሁለቱም ሀገራት ሰላም፣ ስለ ሁለቱም ሀገራት ሕዝቦች አንድነት፣ ስምምነትና የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት በአግባቡ ተጠብቆ ማስቀጠል ስለሚቻልበት ሁኔታ በተመለከተ ሰፊ የሆነ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውንና ፕሬዚዳንቱም ቀና የሆነ የስምምነትና የትብብር መንፈስ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ከላይ የተገለፁ ሐሳቦችን በተመለከተ በመርህ ደረጃ ሙሉ በሙሉ መስማማታቸውንና የሁለቱም ሀገራት ታሪካዊ የሆነ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ጠንካራ ግንኙነት አሁንም በመተማመን ላይ ተመሥርቶ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን በወቅቱ ለመረዳት ተችሏል ፡፡
No comments:
Post a Comment